አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 27 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ዐቃቤ ሕግ እና ፖሊስ ቅንጅታዊ አሠራራቸውን ሊያጎለብቱ እንደሚገባ የፍትሕ ሚኒስትር ዶክተር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ ገለጹ፡፡
የዐቃቤ ሕግና የፖሊስ ተቋማት በተናጠል የሚሰሩት ተግባር ያለ ቢሆንም ፣ የጋራ በሆኑ ጉዳዮች ላይም በትብብርና በቅንጅት መንቀሳቀስ እንዲቻል ቋሚ መድረክ በመፍጠር የወንጀል ምርመራና አጥፊዎችን የማስቀጣት ተግባር አፈጻጸም እየጎለበተ እንዲሄድ መስራት እንደሚያስፈለግም ጨምረው ገልጸዋል፡፡
በተለይም በሚያጋጥሙ ችግሮች ዙሪያ በጥልቀት በመወያየት የመፍትሄ አቅጣጫ በማሰቀመጥ የወንጀል ፍትህ አስተዳደር ተግባር ወደ ተሻለ ደረጃ እንዲደርስ መስራት ይጠበቅብናል ማለታቸውን ከፍትህ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
በውይይት መድረኩ ÷ የፍትሕ ሚኒስቴር፣ የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽንና የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አመራሮች ተገኝተዋል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

