Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ከህዝቡ የተነሱ ችግሮችን በመለየት ምላሽ መስጠት የሚያስችል ዕቅድ አዘጋጅቶ ወደ ሥራ መግባቱን የጋምቤላ ክልል ገለጸ

 

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 28፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በህዝቡ የተነሱ ጥያቄዎችን በመለየት ለተገልጋዩ ህዝብ አፋጣኝ መልስ ለመስጠት ሁሉም ተቋማት የስራ ዘርፋቸውን ሊያጠናክሩ እንደሚገባ የጋምቤላ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኡሞድ ኡጁሉ አሳሰቡ።

በጋምቤላ ከተማ በተደረጉ ህዝባዊ የምክክር መድረኮች ላይ የተነሱ ጥያቄዎችን የሚመልስ ክትትል ማድረጊያ መሪ ዕቅድ መዘጋጀቱ ተገለጿል።

አቶ ኡሞድ ኡጁሉ በመድረኩ ላይ እንንደገለጹት÷ በመሰረተ ልማት፣ በመልካም አስተዳደር፣ በኢኮኖሚና በማህበራዊ ጉዳዮች ላይ ከህዝቡ የተነሱ ችግሮችን በመለየት አፋጣኝ ምላሽ ለመስጠት እንዲያስችል መሪ ዕቅዱ መዘጋጀቱ ተገቢ ነው ብለዋል።

መሪ ዕቅዱን የጋምቤላ ክልል የመንግስት ረዳት ተጠሪ እና የብልፅግና ፓርቲ ፖለቲካ ዘርፍ ሃላፊ አቶ ሩዋች አቅርበዋል፡፡

በመድረኩ ላይ ከፍተኛ አመራሮችን ጨምሮ ከክልሉ ተቋማት የተውጣጡ ባለሙያዎች መገኘታቸውን ከጋምቤላ ክልል ኮሙኒኬሽን ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

 

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version