Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በአፍሪካ 346 ሚሊየን ዜጎች በአስከፊ ረሃብ ውስጥ እንደሚገኙ ተገለፀ

 

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 28፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአፍሪካ 346 ሚሊየን ዜጎች በአስከፊ ረሃብ ውስጥ እንደሚገኙ ዓለም አቀፉ ቀይ መሰቀል ማህበር አስታወቀ፡፡

ግጭት፣ የአየር ንብረት ለውጥ እና የምግብና የነዳጅ ዋጋ መናር ለረሃቡ መከሰት ምክንያት መሆኑን ነው ማህበሩ ያስታወቀው፡፡

ባለፈው ዓመት 286 ሚሊየን ሰዎች ለረሃብ ተጋልጠው እንደነበር ያስታወሰው ማህበሩ፥ አሁን ላይ 346 ሚሊየን አፍሪካውያን በከፋ ረሃብ ውስጥ እንደሚገኙ እና በሚቀጥሉት ወራት ቁጥሩ ሊጨምር እንደሚችል አስታውቋል፡፡

ሶማሊያ፣ ኢትዮጵያ፣ ሞሪታኒያ እና ቡርኪናፋሶ ደግሞ ከፍተኛውን የተጎጅዎች ቁጥር ያስመዘገቡ ሀገራት መሆናቸው ተመላክቷል፡፡

በዩክሬን ያለው ግጭት፣ የምግብ እና የነዳጅ ወጪዎች መጨመር እና የአቅርቦት ሰንሰለት መስተጓጎል እንዲሁም የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ በአህጉሪቱ ኢኮኖሚ ላይ ተፅዕኖ ማድረሳቸውንም ገልጿል፡፡

የማህበሩ ኦፕሬሽን ዘርፍ ሃላፊ ዶሚኒክ ስቲልሃርት እንደተናገሩት አፍሪካውያን ሕፃናት በምግብ እጦት ለተለያዩ በሽታዎች እና ለሞት እየተጋለጡ ነው።

ስለሆነም በሚሊየን የሚቆጠሩ ህፃናትን ለመታደግ ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ወደ ረሃብ ተጎጅዎች ፊቱን ሊያዞር ይገባል ማለታቸውን ፕረስ ቲቪ ዘግቧል፡፡

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version