አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 28 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ አዲስ የተሾሙ የአምስት አገራት አምባሳደሮችን የሹመት ደብዳቤ ተቀበሉ።
በዚህም የዮርዳኖስ፣ የሲሸልስ፣ የኮቲ ዲቯር፣ የቤኒን እና የኮንጎ ሪፐብሊክ አምባሳደሮች የሹመት ደብዳቤን ተቀብለዋል።
ፕሬዚዳንቷ ኢትዮጵያ ከየሀገራቱ ጋር ያላትን የወዳጅነት ትብብር የማጠናከር ፍላጎት እንዳላት መናገራቸውን ከፕሬዚዳንት ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

