አዲስ አበባ፣ መጋቢት 28፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በህልውና ዘመቻው የተገኘውን ውጤት በልማቱ ዘርፍም ለመድገም እየተሠራ መሆኑን የአማራ ክልል የግብርና ቢሮ አስታወቀ፡፡
የቢሮው ኃላፊ ዶክተር ኃይለማርያም ከፋለ ባለፉት ሁለት ወራት ከምርት ስብሰባ በኋላ ወደ ድህረ ምርት በተገባባቸው ሥራዎች፥ በተፋሰስ የንቅናቄ ሥራዎች እና በአጠቃላይ በግብርናው ዘርፍ የተሠሩ ሥራዎች ላይ መግለጫ ሰጥተዋል።
በመግለጫቸውም በ157 ወረዳዎች የተፈጥሮ ሃብት ጥበቃ እና የተፋሰስ ሥራ በሕዝብ ተሳትፎ መሠራቱን አንስተዋል።
ደን ልማትን እና የዘንድሮው የአረንጓዴ አሻራን በተመለከተም የተከላ ቦታ ልየታ 60 በመቶ መጠናቀቁን ጠቁመው÷ ለዚህም 1 ነጥብ 5 ቢሊየን ችግኝ ለተከላ እንደሚዘጋጅ ገልጸዋል፡፡
ይህም በየጣቢያዎቹ የሚዘጋጅ እና ከህብረተሰቡ የሚሰበሰብ መሆኑን ገልጸው÷ እስካሁን ባለው ሁኔታም 800 ሺህ ችግኝ መዘጋጀቱን በመግለጫቸው አንስተዋል፡፡
በለይኩን ዓለም
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

