አዲስ አበባ፣ መጋቢት 28፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ዛሬ ከሳዑዲ አረቢያ 1 ሺህ 103 ዜጎች ተመልሰዋል።
ተመላሾቹ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የቆንስላ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ሰራተኞች እና ሥራ ኃላፊዎች አቀባበል ተደርጎላቸዋል፡፡
ከመጋቢት 21 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ በሳዑዲ አረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ያሉ ዜጎች የመመለሱ ሥራ እየተከናወነ ሲሆን÷እስካሁን የመጡት ሁሉም ተመላሾች ከአዲስ አበባ ወደቀያቸው መላካቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ክልሎችም ተመላሽ ዜጎችን በመቀበል ረገድ ከብሔራዊ ኮሚቴው ጋር በቅንጅት እየሰሩ ነው ተብሏል፡፡ ለዚህም በመኖሪያ አካባቢያቸው መልሶ ለማቋቋም እንቅስቃሴዎችን በማድረግ ላይ ይገኛሉ ነው የተባለው።
በሳዑዲ አረቢያ እስር ቤቶች እና ማዕከላት ያሉ ዜጎችን ወደ ሀገራቸው ለመመለስ 16 መንግስታዊ ተቋማትን በአባልነት ያቀፈ እና በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሰብሳቢነት የሚመራ ብሔራዊ ኮሚቴ ተቋቋሞ ስራውን በመፈፀም ላይ ይገኛል።
በሳምንት ለሶስት ቀናት በቀን ሶስት ጊዜ በሚደረግ በረራ ዜጎችን የመመለሱ ስራ እንደቀጠለ ነው።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

