Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የኦሮ ፍሬሽ የገበያ ትስስር በተመጣጣኝ ዋጋ ምርቶችን እንድናገኝ አድጎናል – ሸማቾች

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 28፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ኦሮ ፍሬሽ የገበያ ትስስር አምራቾች ምርታቸውን ለተጠቃሚው በማቅረባቸው በተመጣጣኝ ዋጋ የግብርና ምርቶችን እንድናገኝ አስችሎናል ሲሉ ሸማቾች ተናገሩ፡፡

ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ቅኝት ባደረገባቸው በሳር ቤትና በጀሞ የኦሮ ፍሬሽ የገበያ ስፍራዎች÷ ተጠቃሚው ትኩስ የግብርና ምርቶችን በተመጣጣኝ ዋጋ ሲገበያይ ውሏል፡፡
ሸማቾችም የግብርና ምርቶችን በተመጣጣኝ ዋጋ በመግዛታቸው መደሰታቸውን ገልጸው÷ የገበያ ትስስሩ በሌሎች አካባቢዎችም እንዲስፋፋና ቀጣይነት እንዲኖረው ጠይቀዋል።
የኦሮሚያ ኅብረት ስራ ኤጀንሲ የግብይት ቡድን መሪ አቶ ተሽቴ ገመዳ÷ የገበያ ትስስሩ የደላላ ጣልቃ ገብነትን በማስወገድ ለህብረተሰቡ ጥራት ያለው ምርት በተመጣጣኝ ዋጋ በማቅረብ የዋጋ ንረትን ለማረጋጋት ከፍትኛ ሚና መጫወቱን ገልጸዋል።
የኦሮሚያ አምራች ማህበራት የሚያመጧቸውን ምርቶች ቀጣይነት ባለው ሁኔታ ለተጠቃሚው ለማቅረብ ከሸማች ማህበራት ጋር በቅንጅት እየሰሩ መሆናቸውንም ተናግረዋል።
የሸማች ማህበራት ዩኒየኖች በሚገነቧቸው የመሸጫ ማዕከላት ምርቶቹ በቋሚነት እንዲቀርቡ የማድረግ እቅድ መኖሩንም ነው አቶ ተሽቴ የተናጉት፡፡
በትዕግስት ስለሺ
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version