Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ለኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን የቦርድ አባላት ሹመት ተሰጠ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 29፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣንን ለማቋቋም በወጣው አዋጅ ቁጥር 1238/2ዐ13 መሠረት የቦርድ አባላት ተሹመዋል፡፡
በዚሁ መሠረት ፡-
1. አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ከውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር – ሰብሳቢ
2. አምባሳደር ናሲሴ ጫሊ ከቱሪዝም ሚኒስቴር – አባል
3. አምባሳደር ሀሰን አብዱልቃድር ከዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማዕከል – አባል
4. ዶክተር አጋረደች ጀማነህ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ – አባል
5. ዶክተር በድሉ ዋቅጅራ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ -አባል
6. ዶክተር መሣይ ገብረማርያም ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ – አባል
7. ዶክተር ወዳጀነህ ማኅረነ አማካሪ – አባል
8. ቀሲስ ታጋይ ታደለ ከሃይማኖት ተቋማት – አባል
9. ኡስታዝ ያሲን ኑሩ ከሃይማኖት ተቋማት አባል ሆነው በ11 ተቃውሞ እና በ17 ድምፀ ተአቅቦ በአብላጫ ድምፅ ሹመታቸው ጸድቋል።
ተሿሚዎቹ ቃለ መሃላ መፈጸማቸውን ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version