Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በኦሮሚያ ክልል ሰላም እና ጸጥታ ላይ ያተኮረ ውይይት ከጸጥታ አካላት ጋር እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 29፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦሮሚያ ክልል ሰላም እና ጸጥታ ላይ ያተኮረ ውይይት ከጸጥታ አካላት ጋር እየተካሄደ ይካሄዳል፡፡

በውይይቱ ላይ የክልሉ የጨፌ አፈ ጉባኤ ሰዓዳ አብዱረህማን የክልሉን ጸጥታ ማረጋጋጥ እና የህዝቡ ስጋት የሆነውን ሸኔን ለማስወገድ እየተሰራ ነው ብለዋል።

በውይይቱ ላይ በሸኔ ላይ እየተወሰደ ያለውን እርምጃ በተመለከተ የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽነር ጄነራል አራርሳ መርዳሳ፥ ሸኔ በሚንቀሳስባቸው ዞኖች መከላከያን እና የፌዴራል የጸጥታ ሃይል ከክልሉ የጸጥታ ሃይል ጋር በመሆን እርምጃ እየወሰዱ ነው ብለዋል።

እየተወሰደ ባለው እርምጃ በአሸባሪው ተይዘው የነበሩ አካባቢዎች ነጻ መውጣታቸዉን ተናግረዋል።

ኮሚሽነር ጄኔራሉ ባቀረቡት ሪፖርት ሸኔ አሁንም የጥፋት ድርጊቱን እየፈጸመ ይገኛል ያሉ ሲሆን ፥ ንጹሃንን መግደል፣ ማፈናቀል እና ንብረት ማውደም የቡድኑ ተግባር ሆኗል ብለዋል።

ለሸኔ መረጃ መስጠትና የሎጂስቲክ ድጋፍ ማድረግ በአንዳንድ የመንግስት መዋቅር ውስጥ ባሉ አመራሮች ይታያል ፤ ይህም እየተወሰደ ያለው እርምጃ ላይ እንቅፋት ፈጥሯል ሲሉም ነው የተናገሩት።

በአዳነች አበበ

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version