አዲስ አበባ፣ መጋቢት 29፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ብልፅግና ፓርቲ ሴቶች ሊግ ጽሕፈት ቤት ለተፈናቃይ ወገኖች ከ11 ሚሊየን ብር በላይ ግምት ያላቸውን ለዋግኽምራ ብሄረሰብ አስተዳደር አስረከበ፡፡
የአዲስ አበባ ብልፅግና ፓርቲ ሴቶች ሊግ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ወይዘሮ የሺ ወልዴ÷ ከተሰበሰበው ገንዘብ ውስጥ ከ11 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመቱ የምግብና ምግብ ነክ ያልሆኑ የተለያዩ ቁሳቁሶችን በዋግኽምራ ለሚገኙ ተፈናቃይ ወገኖች አስረክበዋል፡፡
ተፈናቃዮቹ ወደ ቀያቸው ተመልሰው እስኪቋቋሙ ድረስ ድጋፋችን ይቀጥላል ያሉት ጽ/ ቤቱ ኃላፊ ወይዘሮ የሺ ወልዴ÷ ችግራችሁ ችግራችን ነው፤ በአካል አብረን ባንሆንም በመንፈስ አንድ ነን አይዟችሁ በማለት ተፈናቃዮችን አፅናንተዋል።
የዋግኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ቡድን መሪ ወይዘሮ ዝናሽ ወርቃለም በበኩላቸው ÷ የአዲስ አበባ ብልፅግና ፓርቲ ሴቶች ሊግ ጽ/ቤት ላደረገው ድጋፍ በተፈናቃይ ወገኖች ስም ምስጋና ማቅረባቸውን እና ድጋፉ ተጠናክሮ እንዲቀጥል መጠየቃቸውን ከአዲስ አበባ ብልጽግና ፓርቲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

