Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የሶማሊያ መንግስት በእሳት አደጋ ንብረት ለወደመባቸው ነጋዴዎች የ12 ነጥብ 7 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 29፣ 2014 (ኤፍ ቢሲ) የሶማሊያ መንግስት በሀርጌሳ ከተማ በደረሰው የእሳት አደጋ ንብረታቸው ለወደመባቸው ነጋዴዎች የ12 ነጥብ 7 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ አደረገ፡፡

በሃርጌሳ ከተማ በዋሄን የገበያ ማዕከል በተፈጠረው የእሳት አደጋ 28 ሰዎች አደጋ ሲደርስባቸው ከ1 ነጥብ 5 እስከ 2 ቢሊየን ዶላር የሚገመት ንብረት መውደሙን ሲ ጂ ቲ ኤን በዘገባው አስታውሷል።

ይህን ተከትሎም የሶማሊያ አስተዳደር ከገበያ ስፍራው ቃጠሎ ጋር በተያያዘ የአስቸኳይ ጊዜ ድጋፍ ለማድረስ 2 ቢሊየን ዶላር እንደሚያስፈልገው አስታውቋል።

ንብረታቸው የወደመባቸውን ነጋዴዎች መልሶ ለማቋቋምም የሶማሊያ መንግስት የ12 ነጥብ 7 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ ማድረጉን የሶማሊያ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ካዳር ጉላይድንን ጠቅሶ የሀገሪቱ መገናኛ ብዙሃን ዘግቧል፡፡

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version