አዲስ አበባ፣ መጋቢት 30፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ እና ኬንያ በፖለቲካና ማህበራዊ መስኮች ያላቸውን መልካም ግንኙነት የዜጎችን ህይወት ወደ የሚያሻሽል የኢኮኖሚ ፋይዳ እየተለወጠ መሆኑን በኬንያ የኢትዮጵያ አምባሳደር መለስ ዓለም ገለጹ።
የኢፌዴሪ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር መለስ ዓለም፥ በሁለቱ አገራት መካከል ስላለው ጠንካራና የቆየ ዲፕሎማሲያዊና የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት፣ ኢንቨስትመንት፣ ባህል፣ የመሳሰሉ ማህበራዊ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ጉዳዮች ዙሪያ ገለፃ አድርገዋል።
በሁለቱ አገራት መካከል ለዘመናት የቆየው መልካም የዲፕሎማሲ ግንኙነት የበለጠ ለማጠናከር ዘርፈ ብዙ ስራዎች መስራታቸውን ጠቅሰው ፥ ለዚህም እንደማሳያ የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት በስፖርትና ባህል ዲፕሎማሲ እንዲጠነክር መደረጉን አስረድተዋል ።
የሁለቱ አገራት ህዝቦች ተጠቃሚ የሚያደርግ ውጤት እየመጣ መሆኑን ጠቁመው ፥ የላሙ ወደብ ግንባታ መጠናቀቅ፣ የሞያሌ የአንድ መስኮት የጉምሩክ አገልግሎት መጀመር፣ ሳፋሪኮም እንዲሁም የኬንያ የኃይል ማመንጫ ኬንጄን ኩባንያ ወደ ኢትዮጵያ መግባበት፣ በተመሳሳይ የኢትዮጵያ ባለሃብቶች ኬንያ ውስጥ መዕዋለ-ነዋያቸውን እያፈሰሱ መሆናቸውን አብራርተዋል።
አምባሳደር መለስ ዓለም፥ የኢትዮ-ኬንያ ግንኙነት ላይ ገለፃ ያደረጉት በኬንያ ታዋቂ ከሆነው ካፒታል አፍ.ኤም ራዲዮ ጣቢያ ጋር ባደረጉት ቃለመጠይቅ መሆኑም ተገልጿል።
ኢትዮጵያውያን ኬንያን እንደ ሁለተኛ አገራቸው እንደሚመለከቱ የተናገሩይ አምባሳደሩ ፥ የአገራቱ ዕጣ ፋንታ የተሳሰረ እንደሆነ መግለጻቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

