አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 1፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በሥራ እና ክህሎት ሚኒስቴር እና በአዲስ አበባ ከተማ አሰተዳደር የሥራ ኢንተርፕራይዝ ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ በቅንጅት የሚካሄደው “ብቃት” የወጣቶች የሥራ ላይ ልምምድ የሙከራ ትግበራ አፈፃፀም የጋራ ግምገማ መድረክ ተካሂዷል፡፡
በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የሥራ፣ ሥራ ስምሪት እና ገበያ ዘርፍ ሚኒስትር ዲኤታ አቶ ንጉሡ ጥላሁን በሀገሪቱ ውስጥ በየዓመቱ 2 ሚሊየን ወጣቶች ወደ ሥራ ገበያው እንደሚገቡ አንስተው ፥ ይህንን መመለስ የሚችል ሥርዓት በመዘርጋት ወጣቶችን መደገፍና ሥራ የሚፈጥሩ የግል ባለሃብቶችን ማበረታታት ይገባል ነው ያሉት።
በተለይም በማህበራዊና በኢኮኖሚያዊ ችግሮች ምክንያት ትምህርታቸውን በዩኒቨርሲቲ ፣ በቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች ገብተው መማር ያልቻሉ ወጣቶችን የሚያግዝ ፕሮጀክት ተቀርዖ ወደ ሥራ መገባቱ ለተያዘው ለዜጎች ሥራ ዕድል የማመቻቸት ትግበራ ትልቅ አጋዥ እንደሆነ ሚኒስቴር ዴኤታው አንስተዋል።
ስለሆነም በሙከራ ትግበራ የተገኘው ውጤት ትልቅ ማሳያ ነው ማለታቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
ፕሮጀክቱ በሃገር ደረጃ 70 ሺህ ወጣቶችን ተጠቃሚ የሚያደርግ ሲሆን፥ ከእነዚህ ውስጥ 49 ሺህ በአዲስ አበባ እና 21 ሺህ ደግሞ በሙከራ ደረጃ በክልሎች የሚተገበር እንደሆነም ተነስቷል።
በመሆኑም የዛሬው መድረክ በቀጣይ በአዲስ አበባ ለሚጀመረው ፕሮግራም እና ወደ ክልሎች ለማውረድ የታሰበውን የወጣቶች ሥራ ዕድል ለማመቻቸትና ከግሉ ዘርፍ ጋር ለማስተሳሰር እስከአሁን የተሰሩ ሥራዎችን መገምገምና ለቀጣይ ትግበራ ውጤታማነት በጋራ ማነቆዎችና መፍትሄ አቅጣጫዎች ላይ መግባባት ተገቢ መሆኑ ተገልጿል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

