Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የአፋር ክልል የጤና ኤክስቴንሽን ፕሮግራም ማሻሻያ ፍኖተ ካርታ ይፋ ሆነ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 1፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአፋር ክልል የጤና ኤክስቴንሽን ፕሮግራም ማሻሻያ ፍኖተ ካርታ ላይ ውይይት ሲካሄድ ቆይቶ ዛሬ ይፋ መደረጉን ጤና ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
የጤና ኤክስቴንሽን ፕሮግራም ፍኖተ ካርታው ለ 15 አመታ የሚተገበር ሲሆን÷ ይህም ከፈረንጆቹ 2020 እስከ 2035 ድረስ የሚቆይ እና በየአምስት አመቱ ነባራዊ ሁኔታ እየተከለሰ መሬት ላይ የሚወርድ ይሆናል ተብሏል።
በውይይቱ ወቅት የጤና ሚኒስትር ዲኤታ ዶክተር ደረጃ ዱጉማ የጤና ኤክስቴንሽን ፕሮግራም የቅድሚያ አጀንዳ ተደርጎ ከተሠራ የጤና ስርአቱን ይበልጥ መገንባት ይቻላል ብለዋል፡፡
ለዚህም በየደረጃው ያሉ የሚመለከታቸው አካላት እቅዱን በሚገባ ይዘው ለተግባራዊነቱ ከተረባረቡ የጤና ኤክስቴንሽን ማሻሻያ ፍኖታ ካርታው በጤና ስርአቱ ላይ ትልቅ መሻሻል እንደሚያመጣ ያላቸውን እምነት ገልጸዋል።

የአፋር ክልል ጤና ቢሮ ኃላፊ አቶ ያሲን ሀቡብ የጤና ኤክስቴንሽን ማሻሻያ ፍኖታ ካርታው እስትራቴጂክ እቅድ በክልሉ እውን ለማድረግ እንደሚሰሩ ገልጸው÷ ፕሮግራሙ 18ቱን የጤና ኤክስቴንሽን ፓኬጆች ህብረተሠቡ እንዲጠቀም በማድረግ የራሱን ጤና በራሱ መጠበቅ እንዲችል የሚያግዝ መሆኑን አብራርተዋል፡፡

በተጨማሪም የክልሉ የጤና ሥራዎች በጥናት ላይ ተመስርተው እንዲሠሩ ከአርማወር ሀንሰን የምርመር ተቋም ጋር የጋራ መግባቢያ ሰነድ ተፈራርመዋል።

የአርማወር ሀንሰን የምርምር ተቋም ዋና ዳይሬክተር ፕሮፌሰር አፈወርቅ ካሱ÷ በክልሉ የአርብቶ አደር ጉዳዮችን ለመረዳት እና ለመስራት የተቋሙ ሙያተኞች ወደ ክልሉ ሲመጡ አስፈላጊውን ድጋፍ እንዲደረግላቸው ጠይቀዋል፡፡

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version