አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 1፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ በሁለተኛው የአፍሪካ ኢንተርናሽናል ቴኳንዶ ሻምፒዮና መክፈቻ ቀን ብቻ 11 የወርቅ ሜዳሊያዎች አገኘች።
በኢትዮጵያ አስተናጋጅነት በራስ ኃይሉ ስፖርት ትምህርትና ስልጠና ማዕከል ዛሬ መካሄድ በጀመረው የአፍሪካ ኢንተርናሽናል ቴኳንዶ ሻምፒዮ÷ ኢትዮጵያ፣ ጋምቢያ፣ ሴኔጋል፣ ኡጋንዳ፣ ሶማሊያ፣ ታንዛንያ፣ ኮቲዲቯር፣ ሞዛምቢክ፣ ጅቡቲ፣ ብሩንዲ እና ዚምባቡዌ እየተሳተፉ ነው።
በሻምፒዮናው መክፈቻ ቀን በተካሄዱ የፍጻሜ ውድድሮች ኢትዮጵያ በወንድ 6 በሴት 5 በድምሩ 11 የወርቅ ሜዳሊያዎችን በማግኘት የበላይነቱን ይዛለች።
ከወርቅ ሜዳሊያ በተጨማሪ 11 የብርና 10 የነሐስ በድምሩ 32 ሜዳሊያዎች አግኝታለች፡፡
ሜዳሊያዎቹ የተገኙት በቴኳንዶ ትዕይንት፣ ፍልሚያ እና ‘ፖወር ቴስት’ በተሰኙ የውድድር አይነቶች መሆኑን ኢዜአ ዘግቧል።
ሴኔጋል በሻምፒዮናው መክፈቻ 1 የወርቅ ሜዳሊያ ያገኘች ሲሆን÷ ሞዛምቢክ፣ ኡጋንዳ እና ብሩንዲ ሌሎች ሜዳሊያ ካገኙ ሀገራት ዝርዝር ተካተዋል፡፡
11 አገራት እየተሳተፉበት የሚገኘው 2ኛው የአፍሪካ ኢንተርናሽናል ቴኳንዶ ሻምፒዮና ነገ ፍጻሜውን ያገኛል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

