Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ሚኒስቴሩ የህፃናትን መብትና ደህንነት ለማስጠበቅ የተያዘውን ዕቅድ ለማሳካት ጥረት መደረጉን አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 2፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የህፃናትን መብትና ደህንነት ለማስጠበቅ በበጀት ዓመቱ የተለያዩ አሰራሮችን በመዘርጋት፣ የአቅም ግንባታ እና የግንዛቤ ስራዎችን በመስራት የተያዘውን ዕቅድ ለማሳካት ጥረት መደረጉን የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ገለፀ፡፡
የሚኒስቴሩ፣ የክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች የ9 ወር ሴክተር ጉባዔ “በላቀ ትጋትና ቅንጅታዊ አሰራር የዜጎች ተጠቃሚነት፣ ተሳትፎና ደህንነት ይረጋገጣል” በሚል መሪ ቃል በሀዋሳ ከተማ ማካሄድ ጀምሯል።
የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ወይዘሮ አለሚቱ ኡሞድ÷ ለሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በተሰጠው የ10 ዓመት መሪ እቅድ መሰረት ባለፉት 9 ወራት የሴቶችን ፣ የወጣቶችን ፣የአካል ጉዳተኞችንና የአረጋውያንን ተሳተፎና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በትኩረት ተሰርቷል ብለዋል።
የህፃናትን መብትና ደህንነት ለማስጠበቅም በበጀት ዓመቱ የተለያዩ አሰራሮችን በመዘርጋትና የአቅም ግንባታ እንዲሁም የግንዛቤ ስራዎችን በመስራት የተያዘውን ዕቅድ ለማሳካት ጥረት መደጉንም ነው ሚኒስትር ዴዔታዋ የተናገሩት።
የፆታ እኩልነትን ማስፈን፣ አካል ጉዳተኞችን በሁሉም የኢኮኖሚ ዘርፍ ተሳታፊና ተጠቃሚ ማድረግ፣ አረጋውያን ድጋፍና እንክብካቤ እንዲደረግላቸው ማድረግና መስራት ለሚችሉ ምቹ ሁኔታዎችን ማመቻቸት፣ ለድህንነት ተጋላጭ የሆኑ ዜጎች ከማህበራዊ ችግራቸው እንዲላቀቁ ለማድረግም በሁሉም ዘርፎች ዜጎችን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ስራዎች መከናወናቸውን ጠቁመዋል።
ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በቀሪ ወራትም የቀሩት የእቅድ ስራዎች ለማሳካት ከክልልና ከተማ አስተዳደሮች እንዲሁም ከተጠሪ ተቋማት ጋር በቅንጅት እንዲሚሰራም ገልፀው ለስራው መሳካት የሰላም ጉዳይ ቀዳሚ የሚሰጠው በመሆኑ ሁሉም ሰላምን ለማረጋገጥ የበኩሉን እንዲወጣ አሳስበዋል።
በቢቂላ ቱፋ
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version