Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የእስራኤል የሕክምና ቡድን ለሠብዓዊ ተልዕኮ አዲስ አበባ ይገባል

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 3፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የእስራኤል የሕክምና ቡድን ከሀገሪቷ ፓርላማ አባላት ጋር ለሠብዓዊ ተልዕኮ ዛሬ አዲስ አበባ ይገባል፡፡

1 ዓመት ከ6 ወር ካስቆጠረው በአሸባሪው ህወሓት ከተቀሰቀሰው ግጭት ወዲህ በእስራኤል ዓለም አቀፍ የልማት ድርጅት ጥላ ሥር የእስራኤል የሕክምና ቡድን ከሀገሪቷ ፓርላማ አባላት ጋር ለሠብዓዊ ተልዕኮ አዲስ አበባ እንደሚገባ ኢስራኤል ሃዮም ዘግቧል፡፡

የሠብዓዊ ተልዕኮ ቡድኑ እስከ ሐሙስ ቆይታ እንደሚኖረው ተገልጿል።

ኢትዮጵያዊው የእስራኤል ፓርላማ አባል ጋዲ ይቫርካን የሕክምና ቡድኑ ወደ አዲስ አበባ እንዲመጣ አስተዋጽኦ ማድረጋቸው ታውቋል።

ቡድኑን ጋዲ ይቫርካን ከእስራኤል የፓርላማ ልዑካን ቡድን አባላት ኤሚሊ ሞአቲ እና ቪላዲሚር ቤላይክ ጋር በመሆን ይመሩታል፡፡

የሎጅስቲክ አቅርቦቱን ደግሞ 170 የእስራኤል የግል ኩባንያዎች፣ የመንግስት ኤጀንሲዎች፣ የማኅበራዊ አገልግሎት ተቋማት፣ የትምህርት መርሃ-ግብር ላይ የሚሰሩ የተለያዩ አካላትን በአንድ ጥላ ሥር በማቀናጀት የሚሰራው የእስራኤሉ ዓለም አቀፍ የልማት ድርጅት `ኤስ አይ ዲ እስራኤል` ይሸፍናል ተብሏል፡፡

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version