አዲስ አበባ፣ሚያዚያ 3፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በፈረንሳይ በሚካሄደው የመጨረሻ ዙር ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ በስልጣን ላይ ያሉት ፐሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን እና ማሪን ሌ ፔን ከፍተኛ ፉክክር ያሳያሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡
ለሚያዚያ 16ቱ የፍፃሜ ምርጫ በተደረገው የመጀመሪያ ዙር ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ማክሮን 27 ነጥብ 41 በመቶ ድምፅ ያገኙ ሲሆን፥ ሌ ፔን 24 ነጥብ 3 በመቶ ድምጽ ማግኘት ችለዋል፡፡
የቀኝ አክራሪ የሚባሉት ሴቷ ተወዳደሪያቸው ሌ ፔን በመጀመሪያ ዙር ያስመዘገቡት ውጤት፥ለ 5 ዓመታት ፈረንሳይን በፕሬዚደንትንት የመሩትን ኢማኑአል ማክሮንን አስደንግጧል ነው የተባለው፡፡
በመጀመሪያው ዙር ምርጫ እስከ 14 በመቶ የሚሆነውን ድምፅ ያገኙትና መሸነፋቸውን የተቀበሉት ሌሎቹ እጩዎች ቫለሪ ፔክረሴ፣ አን ሂዳልጎ፣ ያኒክ ጃዶት እና ፋቢየን ሩሰል ፕሬዚዳንት ማክሮን አንዲያሸንፉ ድጋፍ እናደርጋለን ብለዋል፡፡
ሰባት በመቶ ድምፅ ያገኙት እና የፀረ-ፍልሰት ዘመቻ አቀንቃኙ ኤሪክ ዘሙር ደግሞ ማሪን ሌ ፔን እንዲያሽንፉ ድጋፍ እንደሚያደጉ ገልጸዋል፡፡
በፈረንሣይ የምርጫ ሥርዓት መሰረት፥የፕሬዚዳንትነቱን ቦታ ለማረጋገጥ በመጀመሪያ ዙር ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ የተመዘገቡ ድምፆች ወሳኝነት እንዳላቸው አለጀዚራ በዘገባው አስታውሷል፡፡
በ2017 በተካሄደው የምርጫ ውድድርም ሌ ፔን ከፕሬዚዳንት ማክሮን ጋር ተፎካክረው በ66 ለ 34 በሆነ የድምጽ ልዩነት መሸነፋቸው ይታወሳል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!“

