Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ኢትዮ ቴሌኮም እና አማራ ባንክ የሞጁላር መረጃ ማዕከል ኪራይ ስምምነት ተፈራረሙ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 4፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮ ቴሌኮም የሞጁላር መረጃ ማዕከሉን በኪራይ መጠቀም የሚያስችል ስምምነት ከአማራ ባንክ ጋር ተፈራረመ።
በተደረገው ስምምነት ኢትዮ ቴሌኮም አስር “ራኮችን” በኪራይ ያቀረበ ሲሆን÷የባንኩን የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ስርዓት በማዘመን ደረጃውን በጠበቀ የመረጃ ማዕከል አማካኝነት አስተማማኝ አገልግሎት ለመስጠት እንደሚያስችል ተገልጿል፡፡
በቴክኖሎጂ በመታገዝ የፋይናንስ ኢንዱስትሪውን ከፍ የማድረግ አላማን የያዘው አማራ ባንክ የፈፀመው የአጋር ስምምነት ይህን አላማ ለማሳካት እንደ ጅማሮ የሚወስደው መሆኑን የባንኩ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ሄኖክ ከበደ ገልፀዋል።
የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ ወይዘሪት ፍሬህይወት ታምሩ በበኩላቸው÷ የተደረገው ስምምነት ሀብትን በአግባቡ ለመጠቀም ትልቅ ፋይዳ እንዳለው ገልጸዋል።
በሜሮን ሙሉጌታ
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version