አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 5፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የማዕድን ሚኒስትር ኢንጂነር ታከለ ኡማ ከኮሪያው ብረት አምራች ኩባንያ ፖስኮ ኃላፊና ሙያተኞች ጋር በዛሬው ዕለት ውይይት አድርገዋል።
በውይይቱም የኢትዮጵያ የብረት ማዕድንን በመጠቀም የብረትና የብረት ውጤቶችን ለማምረት ለተያዘው ዕቅድ ፖስኮ በገንዘብ፣ በሙያና ቴክኒክ እንዲሁም በአቅም ግንባታ ድጋፍ ለማድረግ መስማማቱ ተገልጿል፡፡
ኢንጂነር ታከለ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት÷በቅርብ ጊዜያትም የአዋጭነት ጥናት፣ የፋብሪካ ተከላና የሰው ሃብት ልማት ስራዎች ላይ ድጋፍ ለማድረግ ከማዕድን ሚኒስቴር ሙያተኞች ጋር ይፋዊ ስራ መጀመሩን ጠቁመዋል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

