አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 6፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አሸባሪው የህወሓት ቡድን ወራራ ባካሄደበት ወቅት ተቋርጠው የነበሩ ኘሮጀክቶች ወደ ሥራ መመለሳቸውን የደሴ ከተማ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ሳሙኤል ሞላልኝ ገለፁ።
ተቋርጠው ከነበሩ የመንገድ ግንባታዎች መካከል ከገራዶ-ኮሽም በር፣ ከሼል ወደ ከተማ አስተዳደሩ የሚወሰደው መንገድ፣ በከተማዋ የሚገኙ የውስጥ ለውሰጥ የአስፋልት መንገዶች እንዲሁም ገራዶ አካባቢ የሚሠራው መናኸሪያን ጨምሮ ሌሎች የልማት ሥራዎች ተጀምረዋል፡፡
ኘሮጀክቶቹን ለማስጀመር የበጀት እጥረት የነበረ ቢሆንም አመራሩ ውሳኔ በማሳለፍ ኘሮጀክቶቹ በባንክ በተገኘ ብድር ስራ እንዲጀምሩ መደረጉን አቶ ሳሙኤል ተናግረዋል።
ከ800 ሚሊየን ብር በላይ የሚያወጡትን የልማት ኘሮጀክቶች በተያዘላቸው ጊዜ እንዲጠናቀቁ ከተማ አስተዳደሩ እንደሚሰራም ተገልጿል።
በራስ አቅም የአስፋልት ንጣፍ መንገዶችን ለመስራትም ከተማ አስተዳደሩ ለአስፓልት መስሪያ የሚያገለግል ግብዓት ማቀነባበሪያ ቦታ ተረክቦ ወደ ሥራ ለመግባት በዝግጅት ላይ መሆኑን አቶ ሳሙኤል አመላክተዋል፡፡
በከድር መሀመድ
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

