Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በመዲናዋ የስነ- ምግባር ችግር በተስተዋለባቸው የደንብ ክትትልና ቁጥጥር ኦፊሰሮች ላይ እርምጃ ተወሰደ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 10፣ 2014 (ኤፍ ቢሲ) የስነ-ምግባር ችግር በተስተዋለባቸው 28 የደንብ ክትትልና ቁጥጥር ኦፊሰሮች ላይ እርምጃ መውሰዱን የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ የደንብ ማስከበር ጽህፈት ቤት አስታወቀ፡፡
የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ደንብ ማስከበር ጽህፈት ቤት በሁሉም ወረዳ ለሚገኙ የደንብ ክትትልና ቁጥጥር ኦፊሰሮች በደንብ 54/2005 ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና በመስጠት ላይ ይገኛል፡፡
ህገ-ወጥነትን በመከላከልና በመቆጣጠር የህግ የበላይነትን ለማስከበር በርካታ ስራዎች ሲሰሩ መቆየታቸውን የጽህፈት ቤቱ ኃላፊ አቶ ደሳለኝ ካሴ ተናግረዋል።
እየተሰጠ ያለው ስልጠናም ኦፊሰሮቹ ለሚፈፅሙት ተልዕኮ ከእውቀትና ስነ-ምግባር አኳያ አቅም እንዲሆናቸው ታስቦ እንደሆነ እንደሆነ መግለጻቸውን ከአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
በበጀት ዓመቱ የስነ-ምግባር ችግር በተስተዋለባቸው ላይ አስተማሪ እርምጃ በመውሰድ ሶስቱ ከስራ እንዲሰናበቱ፣ 25ቱ ደግሞ ከ1 እስከ 2 ወር ደመወዝ እንዲቀጡ መደረጉን አያይዘው ገልፀዋል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version