አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 13፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በሐረሪ ክልል ባለፉት ዘጠኝ ወራት ከ814 ሚሊየን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡን የክልሉ ገቢዎች ቢሮ አስታውቋል፡፡
የቢሮው ሃላፊ አቶ በቀለ ተመስገን በክልሉ በ2014 የበጀት አመት በዘጠኝ ወራት ውስጥ 814 ሚሊየን 726 ሺህ ብር ለመሰብሰብ ታቅዶ 814 ሚሊየን 838 ሺህ ብር መሰብሰቡን ተናግረዋል፡፡
ከተሰበሰበው ገቢ መካከልም 424 ነጥብ 7 ከቀጥታ ታክስ፣ 244 ነጥብ 2 ሚሊየን ቀጥታ ካልሆነ ታክስ፣ 52 ነጥብ 3 ሚሊየን ብር ታክስ ነክ ካልሆኑ ገቢዎች እንዲሁም 93 ነጥብ 4 ሚሊየን ብር ከማዘጋጃ ቤታዊ ገቢ የተሰበሰበ መሆኑን አስረድተዋል፡፡
የተሰበሰበው ገቢ ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀርም የ239 ነጥብ 9 ሚሊየን ብር ብልጫ እንዳለው ነው የጠቆሙት፡፡
ለገቢው ማደግም በተለይም ከግብር አሰባሰብ ጋር በተያያዘ የአገልግሎት አሰጣጥ ስራዎችን ለማጎልበት በመከናወናቸው እና በደረሰኝ አቆራረጥ ላይ የተጠናከረ ክትትልና ቁጥጥር በመደረጉ ነው ብለዋል።
በቀጣይም የክልሉ ገቢን ለማጎልበት እየተከናወኑ የሚገኙ ተግባራት ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ጠቁመዋል።
በክልሉ በበጀት አመቱ 1 ቢሊየን 64 ሚሊየን ብር ገቢ ለመሰብሰብ መታቀዱን ከቢሮው ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

