Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የፈለጉትን ያህል የአፈር ማዳበሪያም ሆነ ዘር እንዳላገኙ የጅማ ዞን አርሶአ ደሮች ተናገሩ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 17፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የጅማ ዞን አርሶአደሮች ለዘንድሮው የበልግና የመኸር እርሻ የማሳ ዝግጅት ቀደም ብለው ቢጀምሩም እስካሁን ከፍላጎታቸው ጋር የሚጣጣም የአፈር ማዳበሪያም ሆነ ዘር እንዳላገኙ ተናገሩ።

ይህ ደግሞ የዘር ወቅትን ያሳልፍብናል የሚል ስጋት እንዳሳዳሳደረባቸው አርሶ አደሮቹ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ገልፀዋል።

የጅማ ዞን ግብርናና ተፈጥሮ ሀብት ልማት ጽህፈት ቤት በበኩሉ፥ ለዞኑ አርሶአደሮች ለማቅረብ ከታቀደው 790 ሺህ ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ ውስጥ 31 በመቶ ብቻ በእጁ መግባቱን ነው ያስታወቀው።

በዞኑ በዘንድሮው የበልግና የመኸር እርሻ ለማልማት ከታቀደው 560 ሺህ ሄክታር መሬት፥ 70 በመቶ የማሳ ዝግጅት መከናወኑንም ጽህፈት ቤቱ ገልጿል።

በሙክታር ጠሃ

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version