አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 26፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሸዋል ኢድ በዓል በሐረር ከተማ ከግንቦት 1 እስከ ግንቦት 3 ቀን እንደሚከበር የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ኤጀንሲ አስታወቀ፡፡
“ከኢድ እስከ ኢድ” ጥሪን ተከትሎ ከተዘጋጁ መርሐ ግብሮች መካከል “የሸዋል ኢድን በሐረር” እና በጅግጅጋ ከተማ የሚካሄደው ‘ሀገረ መንግስት ግንባታና የዳያስፖራው ሚና’ በሚል ርዕስ የተዘጋጀው ሲምፖዚየም ይገኙበታል፡፡
በጅግጅጋ ከተማ የሚዘጋጀው ሲምፖዚየም በመጭው ቅዳሜ ሚያዝያ 20 ቀን 2014 ዓ.ም ከጠዋቱ 3:00 ሰዓት ጀምሮ የሚካሄድ ሲሆን፥ በሐረር ደግሞ የሸዋል ኢድ ከግንቦት 1 እስከ ግንቦት ቀን 3 ድረስ በሐረር ከተማ ይከበራል።
በዚህም ከኢድ እስከ ኢድ ጥሪን ተከትሎ ወደ ሀገር ቤት የመጡ እንግዶችና በመድረኮቹ ላይ መሳተፍ የሚፈልጉ የዳያስፖራ አባላት ቀጥሎ በቀረቡት አድራሻዎች መመዝገብ የሚችሉ መሆኑን ኤጀንሲው ገልጿል፡፡
በስልክ ቁጥሮች (+251 965 34 55 33 ፤ +251 911 91 21 81 ፤ +251 911 46 55 30 ፤ +251 11 558 7473 ፤ +251 11 558 8355 ወይም በነጻ መስመር 9434) መደወል እንደሚችሉም ነው የተገለጸው፡፡
በተጨማሪም በኢሜል ፡- ethiopian.homecoming@mfa.gov.et በመመዝገቢያ ፎርም ፡ –https://forms.gle/KniUKqEwK2d6ujNi7 እንዲሁም በኢትዮጵያ ዳያስፖራ አገልግሎት (ካሳንቺስ) በአካል በመገኘት ተጨማሪ መረጃ ማግኘት እንደሚችሉም ኤጀንሲው አስታውቋል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን፡፡

