Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ኢትዮጵያ እና ጂቡቲ የነዳጅ ማከማቻ ተርሚናል በጋራ መገንባት የሚያስችል ስምምነት ተፈራረሙ

አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 27 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ እና ጂቡቲ የነዳጅ ማከማቻ ተርሚናል በጋራ መገንባት የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ።
የነዳጅ ማከማቻው ግንባታ በጂቡቲ ነጻ ወደቦች ቀጠና የሚካሄድ መሆኑን በጂቡቲ የኢትዮጵያ ኤምባሲ አስታውቋል።
የመግባቢያ ስምምነቱ ሃገራቱ ወደፊት በዘርፉ ለሚያካሂዱት ልማትና ግንባታ ምቹ ሁኔታን ለመፍጠርና ተጨማሪ እድሎችን ለማየት የሚያስችል ነው ተብሏል።

ሃገራቱ ከዚህ ቀደም በተለያዩ መስኮች በትብብር መስራት የሚያስችሉ ስምምነቶችን መፈራረማቸው ይታወሳል።

ባለፈው የካቲት ወር ላይም የሃገራቱ አየር መንገዶች ፣ የጅቡቲ ዓለም አቀፍ ነጻ ቀጠና እና ወደብ ባለስልጣን እንዲሁም የዶራሌ ደረቅ ጭነት ወደብ አገልግሎት በባህር – አየር ሎጅስቲክስ ላይ በጋራ መሥራት የሚያስችላቸውን ስምምነት መፈራረማቸው የሚታወስ ነው።

ሥምምነቱ ቀጠናዊ ትሥሥሩን ይበልጥ በአየር ፣ በየብስ እና በባህር በማሳለጥ በማጠናከር ያላቸውን አጋርነት ያሳድጋል ተብሎለታል፡፡

Exit mobile version