አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 28፣ 2014 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ ከስፔን የትብብር ዋና ስራ አስፈፃሚ ማርዮ ፋነጁልን ጋር ተወያዩ፡፡
በውይይታቸውም ÷ በስፔሽሊቲና ሰብስፔሻሊቲ ስልጠና ፍኖተ ካርታ መሰረት የልዩ ህክምና እና ጤና አገልግሎት አሰጣጥ ስልጠና ላይ በጋራ በመስራት ሊያጠናክሩ በሚችሉባቸው አቅጣጫዎች ዙሪያ መክረዋል፡፡
በኢትዮጵያ የስፔን ኤምባሲ በጤናው ዘርፍ ለሚያደርገው ድጋፍ ዶክተር ሊያ ምስጋና ማቅረባቸውንም ከጤና ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

