Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የብልጽግና ፓርቲ ሴቶች ሊግ ማዕከላዊ ኮሚቴ መደበኛ ስብሰባውን እያካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 8፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የብልጽግና ፓርቲ ሴቶች ሊግ ማዕከላዊ ኮሚቴ መደበኛ ስብሰባውን እያካሄደ ነው።
የሊጉ ማዕከላዊ ኮሚቴ በመደበኛ ስብሰባው ትናንት በሊጉ ስራ አስፈፃሚ ውይይት ተደርጎባቸው በቀረቡለት የግምገማ ውጤቶችና የውሳኔ ሃሳቦች ላይ ተወያይቶ ውሳኔዎችን እንደሚያሳልፍ ይጠበቃል፡፡
በሊጉ አባላት የተከናወኑ የድህረ ጉባዔ ውይይቶች እና የከተማ ግብርና ንቅናቄ አፈፃፀም እንዲሁም የብልፅግና ፓርቲ ሴቶች ሊግ አንደኛ ጉባዔ የዝግጅት ሂደት ማዕከላዊ ኮሚቴው በዝርዝር የሚወያይባቸው አጀንዳዎች መሆናቸውን ከፓርቲው ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
Exit mobile version