Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በፕሪሚየር ሊጉ ሀድያ ሆሳዕና ኢትዮጵያ ቡናን አሸንፏል

አዲስ አበባ፣ግንቦት 8፣2014 (ኤፍ ቢሲ) በ23ኛ ሳምንት የቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ረፋድ ላይ በተደረገ ጨዋታ ሀድያ ሆሳዕና ኢትዮጵያ ቡናን አሸንፏል፡፡

ጨዋታው በሀድያ ሆሳዕና 1ለ 0 አሸናፊነት ሲጠናቀቅ የድል ጎሉን ሳምሶን ጥላሁን በ22ኛው ደቂቃ ላይ በፍፁም ቅጣት ምት አስቆጥሯል፡፡

ሀዲያ ሆሳዕና ከተከታታይ ሽንፈት በኋላ ወደ አሸናፊነት የተመለሰ ሲሆን ነጥቡን 32 በማድረስ 7ኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ ወጥ አቋም ላይ የማይገኘው ኢትዮጵያ ቡና በ 34 ነጥብ 6ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል፡፡

Exit mobile version