አዲስ አበባ፣ ግንቦት 10፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ኤሌክትሪክ ባልደረሰባቸው ከተሞችና መንደሮች ፍትሃዊ የኤሌክትሪክ ተደራሽነትን ዕውን ለማድረግ ዘርፈ ብዙ ሥራዎች እያከናወኑ መሆኑን አስታወቀ፡፡
ተቋሙ በ2014 በጀት ዓመት ባለፉት ዘጠኝ ወራት ውስጥ 125 አዳዲስ የገጠር ከተሞችና መንደሮችን የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉን ገልጿል፡፡
ተቋሙ አገልግሎቱን ለሁሉም ዜጎች ተደራሽ ለማድረግ ከ1997 ዓ.ም ጀምሮ የአገር አቀፍ ኤሌክትሪክ አቅርቦት ፕሮግራም በመቅረፅ በርካታ ሥራዎች ሲያከናውን የቆየ ሲሆን÷ፕሮግራሙ ከመጀመሩ በፊት 667 የገጠር ከተሞች ብቻ የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ነበሩ፡፡
ሆኖም ከ1998 ዓ.ም ጀምሮ በተደረገው ከፍተኛ ፍትሃዊ የኤሌክትሪክ የማዳረስ ሥራ እስከ መጋቢት 30 ቀን 2014 ዓ.ም ድረስ 7 ሺህ 892 የገጠር ከተሞችንና መንደሮች ኤሌከትሪክ አገልግሎት ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉ ተመላክቷል፡፡
ተቋሙ በተመሳሳይ በ2012 በጀት ዓመት 308፣ በ2013 በጀት ዓመት ደግሞ 341 አዳዲስ የገጠር ከተሞችና መንደሮችን የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉን የአገር አቀፍ ኤሌክትሪክ አቅርቦት ፕሮግራም ዳይሬክተር አቶ ሁሴን መሀመድ ገልፀዋል፡፡
አዳዲስ የገጠር ከተሞችና መንደሮችን የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ለማድረግ ሲታቃድ ዕድሉን የሚያገኙ አካባቢዎች ለይተው እንዲያሳወቁ የሚደረጉት ክልሎች መሆናቸውና እነሱ ቅድሚያ ይሰጣቸው ብለው ለይተው ሲያሳውቁ ሥራው እንደሚከናወን መጠቆሙንም ከአገልግሎቱ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በጋራ በመሆን በብሄራዊ ኤሌክትሪፊኬሽን ፕሮግራም እ.ኤ.አ በ2025 ከዋናው ግሪድ 65 በመቶ እንዲሁም በአማራጭ የኃይል ምንጮች 35 በመቶ የሚሆነውን ህብረተሰብ የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ለማድረግ ጥረት እያደረገ መሆኑ ይታወቃል፡፡

0
People reached
84
Engagements
Boost post
79
5 Comments
Like
Comment
Share