Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የአሰላ ሪፈራልና የማስተማሪያ ሆስፒታል ከ70 ሚሊየን ብር በላይ የሚያወጣ የቁሳቁስ ድጋፍ አገኘ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 25፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በአርሲ ዩኒቨርስቲ የአሰላ ሪፈራልና የማስተማሪያ ሆስፒታል ከ70 ሚሊየን ብር በላይ የሚያወጣ ድጋፍ አገኘ።

 
ድጋፉ ከስዊድኑ “ሂዩማን ብሪጅ” ከተሰኘ ግብረሰናይ ድርጅት የተገኘ መሆኑ ተገልጿል።
 
የተደረገው ድጋፍ በ200 ሚሊየን ብር ወጪ ለተገነባው ሪፈራልና የማስተማሪያ ሆስፒታል የሚውሉ ሙሉ የህክምና ቴክኖሎጂዎችና ቁሳቁሶች መሆናቸውን የዩኒቨርስቲው ፕሬዚዳንት ዶክተር ዱጉማ አዱኛ ተናግረዋል።
 
የሂዩማን ብሪጅ ኢትዮጵያ ዳይሬክተር ኢንጅነር አዳሙ አንለይ በበኩላቸው÷ ድጋፉ የእናቶችና ህፃናትን ሞት ለመቀነስ ከፍተኛ አስተዋፅኦ የሚያበረክት መሆኑን ጠቁመዋል።
 
ሆስፒታሉ ከ3 ነጥብ 5 ሚሊየን በላይ ለሚሆኑ የአርሲና አካባቢው ነዋሪዎችን አገልግሎት ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል።
በአፈወርቅ እያዩ

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

Exit mobile version