አዲስ አበባ ፣ የካቲት 25 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ባለፉት አምስት ቀናት ግምታዊ ዋጋቸው 31 ሚሊየን 614 ሺህ 620 ብር የሚገመት የወጪና ገቢ የኮንትሮባንድ ዕቃዎች ተያዙ።
የተያዙት እቃዎች አዳዲስና አሮጌ አልባሳትና ጫማዎች፣ የአይን መነጽሮች፣ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ ጊዜ ያለፈባቸው ምግቦች፣ የመዋቢያ ቁሳቁሶች፣ ሕገ ወጥ የጦር መሳሪያዎች፣ ተሽከርካሪዎችን ጨምሮ የተለያዩ እቃዎች ናቸው።
እቃዎቹ በቦሌ አየር መንገድ፣ በባህር ዳር፣ ጅማ፣ ሁመራ፣ ድሬዳዋ፣ ሞያሌ፣ አዋሽ፣ ጋምቤላ እና ምዕራብ ሐረርጌ ዞን ሂርና ወረዳ መያዛቸውን ከገቢዎች ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
በተጨማሪም 161 ሺህ 513 የአሜሪካ ዶላር በድሬዳዋ፣ ሁመራ፣ በቶጎ ጫሌ እና በጅግጅጋ በኩል በሕገ ወጥ መንገድ ሲያንቀሳቅሱ የነበሩ ተጠርጣሪዎችም በቁጥጥር ስር ውለዋል።
ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

