Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ውጤታማ የሆኑ ከ700በላይ አንቀሳቃሾች የደረጃ ሽግግር አደረጉ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 14፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ)በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ከ500 ሺህ ብር በላይ ካፒታል ያስመዘገቡ 14 አንቀሳቃሾች ከጥቃቅንና አነስተኛ ዘርፍ ወደ ታዳጊ መካከለኛ ባለሀብትነት ተሸጋገረዋል።

የዞኑ ስራና ስልጠና መምሪያ ሀላፊ አቶ ደሴ ጥላሁን እንደተናገሩት? በዞኑ አቅም የፈጠሩ አንቀሳቃሾች በተለያዩ ጊዜያት የደረጃ ሽግግር ሲያደርጉ ቆይተዋል።

ባለፉት ዓመታት 197 ኢንተርፕራይዞች ወደ ታዲጊ መካከለኛ ባለሀብትነት ተሸጋግረዋል ያሉት ሀላፊው በኢንቨስትመንት ዘርፍ ተሰማርተው ለበርካቶች የስራ እድል መፍጠር መቻላቸውንም ተናግረዋል።

በዚህ ዓመት 711 ኢንተርፕራይዞች ከጀማሪ አንቀሳቃሽ ወደተለያዩ የኢንተርፕራዝ ደረጃዎች የተሻገገሩ ሲሆን ከ500 ሺህ እስከ 1 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር ያስመዘገቡ 14 ኢንተርፕራይዞች ወደ ባለሀብት ተሸጋግረዋል።

በቀጣይ ለኢንተርፕራዞች የኢንቨስትመንት ቦታ ፣ብድርና የማሽን አቅርቦት ተጠቃሚ እንዲሆኑ ይደረጋል ተብሏል።

በተያያዘ በቆላድባ ከተማ 68 አንቀሳቃሾች ወደ ተለያዩ ደረጃዎች እንዲሸጋገር ተደርጓል።

በምናለ አየነው

Exit mobile version