Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ እና አቶ ደመቀ መኮንን የማዕድን ጋለሪን ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 14፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ፣ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን እና ሌሎች ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች የማዕድን ሚኒስቴር ሪፎርም ስራዎችንና የማዕድን ጋለሪን ጎብኙ፡፡

የማዕድን ሚኒስትር ኢንጂነር ታከለ ኡማ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው እንዳሰፈሩት÷ ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ እና አቶ ደመቀ መኮንን ጨምሮ የኢፌዴሪ የቀድሞ ፕሬዚዳንት ሙላቱ ተሾመ እና የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የቀድሞ አፈጉባኤ ኦቦ አባዱላ ገመዳ እንዲሁም ሌሎች የስራ ኃላፊዎች ከተለያዩ አመራሮች ጋር በመሆን የሚኒስቴሩ የሪፎርም ስራዎችንና የማዕድን ጋለሪን ጎብኝተዋል።

ሚኒስትሩ እንዳሉት ፥ የማዕድን ዘርፍ ስራዎች የኢትዮጵያ ከፍታን በሚመጥነው ልክ ማሳደግን መዳረሻ ያደረገ ነው ያሉ ሲሆን ፥ የሪፎርም ስራዎቻችንም ከዚህ ጋር በተናበበ መልኩ ተጠናክረው ይቀጥላሉም ነው ያሉት።

Exit mobile version