አዲስ አበባ፣ግንቦት 15፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የስራ እና ክህሎት ሚኒስቴር ኢትዮጵያ ከኬንያ እና ከታንዛኒያ ጋር በቴክኒክና ሙያ ትምህርት ስልጠና ዘርፍ በጋራ ለመስራት የሚያስችል ስምምነት ሊያፀድቅ መሆኑ ተገለፀ።
የስራና ክህሎት ሚኒስቴር ዴኤታ አቶ አሰግድ ጌታቸው እንደተናገሩት÷ ቴክኒክ እና ሙያ ስልጠና ተደራሽነትን በማስፋት እና ቀጠናዊ ትስስርን ለማጠናከር ከኢትዮጵያ፣ከታንዛኒያ እና ከኬንያ የተመረጡ የቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ተቋማት በተጠቀሱት ሀገራት በመዘዋወር እንዲሰሩ የሚያደርግ ፕሮጀክት መሆኑን ገልፀዋል።
ሶስቱ ሀገራት ባላቸው የየራሳቸው ቴክኒክ እና ሙያ ስልጠና የትምህርት ስርዓት ፖሊሲ በማስተማር በሶስቱ ሀገራት የሚሰሩበት ሁኔታን የሚያመቻች እንደሆነም ተገልጿል።
በሶስቱ ሀገራት የተጀመረው የክህሎት ስልጠና ትስስር የምስራቅ አፍሪካ ሀገራትን በማካተት የሚቀጥል እንደሆነ በውይይቱ ላይ ተነስቷል።
በቅድስት ተስፋዬ

