Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በሰሜን ሸዋ ዞን በ6 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር ወጪ ለሚገነባ ፕሮጀክት የመሰረት ድንጋይ ተቀመጠ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 19፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን በ6 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር ወጪ ለሚገነባ ፕሮጀክት የመሰረት ድንጋይ የማስቀመጥ ስነ-ስርዓት ተካሄደ።
በዞኑ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት መምሪያ በአንጎለላና ጠራ ወረዳ ጨኪ ቀበሌ ጀር የምግብ ማቀነባበሪያ ፋብሪካ በ6 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር ወጪ ፕሮጀክት ሊገነባ መሆኑ ተገልጿል።
በዛሬው እለትም የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ግርማ የሺጥላ በተገኙበት የመሰረተ ድንጋይ የማስቀመጥ ስነስርአት ተከናውኗል።
ፕሮጀክቱ ተመጋጋቢነት ያላቸው 11 ፋብሪካዎችን የያዘ ሲሆን ምግብና ምግብ ነክ ነገሮችን እንደሚያመርት መገለጹን ከአማራ ክልል ብልጽግና ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
Exit mobile version