አዲስ አበባ፣ ግንቦት 19፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በምስራቅ ጎጃም ዞን ደጀን ከተማ ዛሬ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የአምስት ሰዎች ህይወት ማለፉን የዞኑ ፖሊስ መምሪያ አስታውቋል፡፡
አደጋው ዋልያ የህዝብ ማመላለሻ አውቶብስ ከደብረታቦር ወደ አዲስ አበባ በመጓዝ ላይ እያለ በተቃራኒ አቅጣጫ ከደጀን ወደ ቢቸና ይጓዝ ከነበረ አነስተኛ የህዝብ ማመላለሻ ሚኒባስ ጋር ፊት ለፊት በመጋጨቱ ነው የተከሰተው፡፡
በተፈጠረው አደጋም አንድ እግረኛ ሴት፣ከባሱ ውስጥ አንድ ወንድ ህፃን እና ከሚኒባሱ አሽከርካሪውን ጨምሮ 3 ወንዶች በአጠቃላይ የአምስ ሰዎች ህይወት አልፏል፡፡
በተጨማሪም በአደጋው 11 ሰዎች ከባድ እና ቀላል ጉዳት ደርሶባቸው ወደ ደብረ ማርቆስ ሪፈራል ሆስፒታል እና ደጀን የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ለህክምና መላካቸውን ተገልጿል፡፡
በንብረት ላይም ከባድ ጉዳት የደረሰ መሆኑንና የአደጋው መንስኤም በፓሊስ እየተጣራ መሆኑን ከምስራቅ ጎጃም ዞን ፓሊስ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

