አዲስ አበባ፣ ግንቦት 20፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በምሥራቅ አፍሪካ ሀገራት መካከል ሲካሄድ በነበረው የታዳጊ አትሌቶች ሻምፒዮና ኢትዮጵያ በአሸናፊነት አጠናቀቀች፡፡
በ8 የምሥራቅ አፍሪካ ሀገራት መካከል ሲካሄድ በቆየው ከ18 እና ከ20 አመት በታች የሆኑ ታዳጊ አትሌቶች ሻምፒዮና ኢትዮጵያ ቀዳሚዋ ሀገር ሆናለች፡፡
በውድድሩ ኢትዮጵያ በ17 ወርቆች፣ በ3 ብሮች፣ በ2 ነሃሶች፣ እናበ2 ዲፕሎማዎች በከፍተኛ የሜዳልያ ብዛትና ልዩነት በመያዝ በቀዳሚነት ተቀምጣለች፡፡
ቡድኑ ነገ እሁድ ከማለዳው 12:55 ላይ ቦሌ አለም አቀፍ አውሮፕላን ጣቢያ ይደርሳል ተብሎ እንደሚጠበቅ ከአትሌቲክስ ፌዴሬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡