Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ዋልያዎቹ ከሌሴቶ አቻቸው ጋር በአቻ ውጤት ተለያዩ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 22፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ብሄራዊ እግር ኳስ ቡድን ከሌሴቶ አቻው ጋር ባደረገው ሁለተኛ የአቋም መለኪያ ጨዋታ አንድ አቻ ተለያይቷል፡፡

በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ ዋልያዎቹ በ38ኛው ደቂቃ በዳዋ ሆቴሳ አማካኝነት የመጀመሪያውን ግብ አስቆጥረዋል፡፡

ጃኒ ታባሲቶ ደግሞ የሌሴቶ ብሄራዊ ቡድንን አቻ ያደረገችዋን ጎል ጨዋታው በተጀመረ 71ኛው ደቂቃ ላይ አስቆጥሯል፡፡

ሁለቱ ብሔራዊ ቡድኖች ቅዳሜ ዕለት ባከናወኑት የመጀመሪያ የአቋም መለኪያ ጨዋታ በተመሳሳይ አንድ አቻ በሆነ ውጤት መለያየታቸው ይታወሳል፡፡

ፎቶ -ሶከር ኢትዮጵያ

Exit mobile version