Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ዶክተር ኢንጅነር ሀብታሙ ኢተፋ በቦንጋ ከተማ  እየተገነባ ያለውን የንፁህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክትን ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 23፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ዶክተር ኢንጅነር ሀብታሙ ኢተፋ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ቦንጋ ከተማ እየተገነባ ያለውን የንፁህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክት ጎበኙ።

ጉብኝቱ በክልሉ በግንባታ ሂደት የሚገኙ የንፁህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክቶች አፈፃፀም አስመልክቶ የሚካሄደው ውይይት አካል መሆኑ ተገልጿል፡፡

ዶክተር ኢንጂነር ሀብታሙ ቦንጋ ከተማ ሲደርሱ  የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ኢንጅነር ነጋሽ ዋጌሾን ጨምሮ ሌሎች በየደረጃው ያሉ አመራሮች አቀባበል አድርገውላቸዋል።

ቦንጋ ከተማ በንፁህ መጠጥ ውሃ እጦት ተደጋጋሚ ቅሬታ ከሚቀርብባቸው ከተሞች አንዷ መሆኗን ኢዜአ ዘግቧል።

ለችግሩ እልባት ለመስጠት የንፁህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክት በመተግበር ላይ ሲሆን÷ በሚካሄደው ውይይትም በፕሮጀክቱ አፈፃፀም ላይ ላጋጠሙ ችግሮች ውሳኔ እንደሚቀመጥ ይጠበቃል፡፡

የውሀና ኢነርጂ ሚኒስቴር ለመስክ ስራ የሚውሉ አራት ሞተር ሳይክሎች እና 10 ላፕቶፕ ኮምፒውተሮች ድጋፍ አድርጓል።

Exit mobile version