Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ካሪም ቤንዜማ የቻምፒየንስ ሊጉ ምርጥ ተጫዋች ሆኖ ተመረጠ

 

አዲስ አበባ፣ግንቦት 23፣2014 (ኤፍ ቢሲ) የሪያል ማድሪዱ የፊት መስመር አጥቂ ካሪም ቤንዜማ የውድድር አመቱ የቻምፒየንስ ሊጉ ምርጥ ተጫዋች ሆኖ ተመርጧል፡፡

ፈረንሳዊው አጥቂ ክለቡ ሪያል ማድሪድ ለ14ኛ ጊዜ የአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግን በማንሳት ክብረ ወሰኑን ይዞ እንዲቆይ ትልቅ አስተዋፅኦ አድርጓል።

በመድረኩም 15 ጎሎችን በማስቆጠር የውድድሩ ከፍተኛ ጎል አግቢ ሆኖ ጨርሷል።

ከዚህ ባለፈም ቡድኑ የላሊጋን ዋንጫ እንዲያነሳ አስተዋፅኦ ማድረጉ አይዘነጋም፡፡

Exit mobile version