አዲስ አበባ፣ ግንቦት 25፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮ ቴሌኮም በአገር አቀፍ ደረጃ 66 ትምህርት ቤቶችን ተጠቃሚ የሚያደርግ የዲጂታል ትምህርት ማዕከል ፕሮጀክት አስጀመረ፡፡
ኢትዮ ቴሌኮም በአዲስ አበባ ከፍተኛ 23 ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የዲጂታል ትምህርት ማዕከላት ፕሮጀክት አስጀምሯል፡፡
የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ ፍሬህይወት ታምሩ በዚሁ ወቅት እንደገለጹት÷ ተቋሙ ጂታል ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ እየሰራ ነው፡፡
ተማሪዎች በትምህርት ቤቶች ቴክኖሎጂን በማወቅ ቢያድጉ ውጤታማ እንደሚሆኑ ጠቅሰው÷ በዲጂታል ትምህርቱ 140 ሺህ 596 ተማሪዎች ተጠቃሚ ይሆናሉ ብለዋል፡፡
ፕሮጀክቱ ተግባራዊ የሚሆነው በክልሎች በ48 ትምህር ቤቶች እና በአዲስ አበባ ደግሞ በ18 ትምህርት ቤቶች መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ትምህርት ቤቶቹ ከዚህ በፊት የመሠረተ ልማት ችግር ያለባቸው ሲሆኑ÷ በቀጣይ ከኢትዮ ቴሌኮም ስልጠና እንደሚያገኙ ኢዜአ ዘግቧል፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

