Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

 የኢትዮጵያ የማዕድን ማሳያ ተመረቀ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 27፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በማዕድን ሚኒስቴር የሚገኘው የኢትዮጵያ የማዕድን ማሳያ (ጋለሪ) ተመርቆ ተከፍቷል።

የማዕድን ማሳያው በኢትዮጵያ በርካታ ማዕድናት መገኘታቸውን የሚጠቁም እና በየትኛው አከባቢ ምን አይነት ማዕድን እንዳለ መረጃ የሚሰጥ ሲሆን÷ ከዛሬ ጀምሮ ለእይታ ክፍት ይሆናል ተብሏል፡፡

የማዕድን ሚኒስትር ኢንጂነር ታከለ ኡማ ÷ ማሳያውን ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት፣ ለባለሀብቶች፣ ለአምባሳደሮችና ለውጭ የማዕድን ካምፓኒ ተወካዮች ጋለሪውን አስጎብኝተዋል።

ለኢትዮጵያ የማዕድን ዘርፍ ያለው ሀሳብ ከተቋማዊ ሪፎርም ጀምሮ በተግባር እየተገለጠ መሆኑን ጠቅሰው÷ የምንሰራቸው የሪፎርም ስራዎች የኢትዮጵያን የማዕድን ዘርፍ በሚገባው ቦታ ላይ ለማስቀመጥ ነው ብለዋል፡፡

ማሳያውን በይፋ የከፈቱት የማዕድን ሚኒስትር ዴኤታ አቶ  ሚሊየን ማቲዎስ ÷ ማሳያው ኢትዮጵያ በርካታ ማዕድናት እንዳሏት መረጃ የሚሰጥ ነው ብለዋል።

በታሪኩ ለገሰ

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

Exit mobile version