Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

አገራዊ የምክክር ኮሚሽኑ በድሬዳዋ ከሚገኙ የተለያዩ አካላት ጋር ውይይት አካሄደ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 30፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአገራዊ ምክክር ኮሚሽን በድሬዳዋ አስተዳደር ከሚገኙ የሃይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎችና አባ ገዳዎች ጋር ውይይት አካሄደ።
ውይይቱ ኮሚሽኑ እያከናወነ ያለውን ተግባር በማስገንዘብ በቀጣይ አብሮ ለመስራት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ መግባባት ለመፍጠር መሆኑን አምባሳደር መሀሙድ ድሪር ገልጸዋል።
አገራዊ የምክክር ኮሚሽኑ በሦስት ወራት ውስጥ ከተለያዩ አካላት ጋር ውይይት ማድረጉ የተገለጸ ሲሆን÷ ኮሚሽኑ የሚያከናውናቸውን ተግባራት እንደሚደግፉ የውይይቱ ተሳታፊዎች ገልጸዋል።
ውይይቱ በቀጣይ አብሮ ለመስራት ምቹ ሁኔታ ሊፈጥር እንደሚችል መገለጹን ከድሬዳዋ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
አካታችነት፣ ግጽነት፣ ተዓማኒነት፣ መቻቻልና መከባበር፣ብሔራዊ ጥቅም እና ሌሎች ነጥቦች የኮሚሽኑ ምሰሶዎች መሆናቸውም በዚሁ ጊዜ ተገልጿል።
የውይይቱ ተሳታፊዎች በበኩላቸው የሃይማኖት ተቋማት በሚገባቸው ደረጃ ኃላፊነታቸውን እንዳልተወጡ ጠቅሰው፥ ኮሚሽኑ በቀጣይ ለሚሰራቸው ስራዎች እገዛ እንደሚያደርጉ ተናግረዋል።
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version