Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

አሜሪካ በምስራቅ አፍሪካ የበረሃ አንበጣን ለመከላከል ተጨማሪ የ10 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ ይፋ አደረች

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 27 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የአሜሪካው ዓለም አቀፍ ተራድኦ ድርጅት (ዩ ኤስ ኤይድ) በምስራቅ አፍሪካ የበረሃ አንበጣን ለመከላከል ለሚደረገው ጥረት ተጨማሪ የ10 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ ይፋ አደረገ።

የአሁኑ ድጋፍ ኢትዮጵያን ጨምሮ በኬንያ እና ሶማሊያ የበረሃ አንበጣን መስፋፋት ለመግታት ለሚደረገው ጥረት የሚውል ነው ተብሏል።

ድጋፉ የበረሃ አንበጣውን ለመከላከልና ለመቆጣጠር እንደሚውል ተገልጿል።

ከዚህ ባለፈም የበረሃ አንበጣው ጉዳት ባደረሰባቸው አካባቢዎች የሚገኙ ነዋሪዎች ላይ አወንታዊ ለውጥ ያመጣል ተብሎም ይጠበቃል።

ዛሬ ይፋ የተደረገው ድጋፍ የአሜሪካ መንግስት በምስራቅ አፍሪካ የተከሰተውን የአንበጣ መንጋ ለመከላከል ያደረገውን ድጋፍ ወደ 19 ሚሊየን ዶላር ያሳድገዋል።

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

Exit mobile version