Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮች ፣የዓለም አቀፍ ድርጅቶች እና ተቋማት የሥራ ኃላፊዎች በመዲናዋ የተለያዩ ፕሮጀክቶችን ጎበኙ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 3፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አዲስ አበባ የሚገኙ የተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮች ፣የዓለም አቀፍ ድርጅቶች እና ተቋማት የሥራ ኃላፊዎች በአዲስ አበባ ከተማ የተለያዩ ፕሮጀክቶችን ጎበኙ፡፡

አምባሳደሮች ፣የዓለም አቀፍ ድርጅቶች እና ተቋማት የሥራ ኃላፊዎች የአብርሆት ቤተ መፃህፍትን ፣ አንድነት ፓርክን ፣በጠቅላይ ሚኒስቴር ፅ/ቤት እየተከናወነ ያለውን ሞዴል የገፅ ምድር ልማት ናሙና አግድም እርሻ እና ጓሮ አትክልት ጎብኝተዋል፡፡

እንዲሁም የማዕድን ሚኒስቴርን የማዕድን ማሳያ ማዕከልን ጨምሮ ሌሎች ፕሮጀክቶችን ተዘዋውረው መጎብኘታቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

Exit mobile version