Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ከንቲባ አዳነች ከአፍሪካ ኅብረት የልማት ኤጀንሲ ዋና ሥራ አሥፈፃሚ ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 4፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ የአፍሪካ ኅብረት የልማት ኤጀንሲ ዋና ሥራ አሥፈፃሚ ወይዘሮ ናርዶስ በቀለን በፅሕፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል፡፡
 
ከንቲባ አዳነች ለአፍሪካ ኅብረት የልማት ኤጀንሲ ዋና ሥራ አሥፈፃሚ ወይዘሮ ናርዶስ የሀገሪቱን የለውጥ እንቅስቃሴ በተለይም በመዲናዋ እየተከናወኑ ያሉ የለውጥና የሪፎርም ስራዎች ስላሉበት ደረጃ ማብራርያ ሰጥተዋል፡፡
 
በፈተናዎች ውስጥ አልፎ በርካታ የዜጎችን ህይወት የሚቀይር፤ የከተማችንን ጎስቋላ ገፅታ የሚያድስ ስራ እየተሰራ መሆኑንም ገልፀዋል፡፡
 
ወ/ሮ ናርዶስ በቀለ በበኩላቸው÷በአገሪቱ እየተካሄደ ያለውን የለውጥ እንቅስቃሴ ተስፋ ሰጪ መሆኑን ገልፀው÷ በተመለከቱት ነገር በእጅጉ መደሰታቸውን ተናግረዋል፡፡
 
ከንቲባ አዳነች ዘመናዊ የጥቁር ህዝቦች ኩራት መታሰቢያ የሆነውን የአድዋ ሙዚዬምና የማዘጋጃ ቤት ህንፃ እድሳት ስራን ለወይዘሮ ናርዶስ ማስጎብኘታቸውን ከከንቲባ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
 
 
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version