አዲስ አበባ፣ ሰኔ 4፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የምግብ እርዳታ የጫኑና እስካሁን ከተላከው ከፍተኛውን መጠን የያዙ 308 ተሽከርካሪዎች በዚህ ሳምንት ትግራይ ክልል መግባታቸውን የዓለም ምግብ ፕሮግራም አስታወቀ።
የዓለም ምግብ ፕሮግራም በኢትዮጵያ በማህበራዊ ትስስር ገጹ እንዳስታወቀው÷ በዚህ ሳምንት እስካሁን ወደ ትግራይ ክልል ከተላከው ከፍተኛ የሆነውና የምግብ እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው ተጨማሪ 800 ሺህ ሰዎች ተደራሽ የሚሆን ሰብዓዊ ድጋፍ ትግራይ ክልል ገብቷል፡፡
በዚህም የሰብዓዊ እርዳታ የጫኑ 308 ተሽከርካሪዎች ትግራይ ክልል መድረሳቸው ነው የተገለጸው፡፡
የተላከው ሰብዓዊ እርዳታም በክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች ችግር ውስጥ የሚገኙ 800 ሺህ ዜጎችን ተደራሽ ለማድርግ እንደሚያስችል ተመላክቷል፡፡
የዓለም የምግብ ፕሮግራም በአማራ እና አፋር ክልሎች ችግር ውስጥ ለሚገኙ ዜጎች የሚያደርገውን የምግብ እርዳታ በቅርቡ ማሰራጨት እንደሚጀምርም አስታውቋል፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

