Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

አማራ ባንክ አክሲዮን ማህበር ሰኔ 11 ቀን 2014 ዓ.ም ሥራ እንደሚጀምር አስታወቀ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 6 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አማራ ባንክ የአክሲዮን ማህበር ሰኔ 11 ቀን 2014 ዓ.ም ሥራውን በይፋ እንደሚጀምር አስታወቀ።
 
የባንኩን ስራ የመጀመር ሂደትን አስመልክቶ የባንኩ ከፍተኛ አመራሮች መግለጫ ሰጥተዋል።
 
ከ6 ቢሊየን 516 ሚሊየን ብር በላይ በተከፈለ የመነሻ ካፒታል እንዲሁም ከ4 ቢሊየን 825 ሚሊየን ብር በላይ በሆነ ገንዘብ ተጨማሪ አቅም በማሳደግ ባንኩ ለስራ ዝግጁ መሆኑን የባንኩ የቦርድ ሊቀመንበር አቶ መላኩ ፈንታ ገልጸዋል።
 
ባንኩ በ70 ቅርንጫፎች ስራውን የሚጀምር ሲሆን እስከ ሰኔ 30 ቀን 2014 ዓ.ም ድረስ የቅርንጫፍ ቁጥሩን ወደ 100 ለማሳደግ አቅዷል።
 
ባንኩ በኢትዮጵያ የባንክ ኢንዱስትሪ ውስጥ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ባለአክሲዮን መሆኑንም ነው የገለጹት፡፡
 
ከመደበኛው የፋይናንስ አገልግሎት በተጨማሪ “ከባንክ ባሻገር” በሚል የማህበረሰቡን ሕይወት ለማሻሻል የተለያዩ አማራጮችን እንዳዘጋጀ መጠቆማቸውንም ኢዜአ ዘግቧል፡፡

 

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

Exit mobile version