Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

አረንጓዴ ዐሻራ ለቀጣዩ ትውልድ የምናወርሰው ሀብት ነው- አቶ ደመቀ መኮንን

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 14፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አረንጓዴ ዐሻራ ለቀጣዩ ትውልድ የምናወርሰው ሀብት ነው ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ገለጹ።
ባለፉት አመታት በአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር አበረታች ውጤት መገኘቱንም አንስተዋል።
አቶ ደመቀ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለጹት÷ ኢትዮጵያ በአረንጓዴ ዐሻራ የሰራችው ስራ ለተቀረው ዓለም ምሳሌ የሚያደርጋት ነው፡፡
የአየር ንብረት ለውጥ ለምድራችን ፈተና በሆነበት ወቅት ችግኝ መትከልንና መንከባከብን ባህል ልናደርግ ይገባልም ነው ያሉት፡፡
ሁሉም ኢትዮጵያውያን ለዘንድሮው የአረጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር ስኬት እንዲሰሩም ጥሪ አቅርበዋል።
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ በአረንጓዴ ዐሻራ የመክፈቻ መርሐግብር አረንጓዴ ዐሻራቸውን አስቀምጠዋል።
በአፈወርቅ እያዩ
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version